#ፊደል_ማርያም

Опубликовано: 14 Январь 2025
на канале: Deacon Zemari Kedametsega Yohanis
43,837
989

#ፊደል_ማርያም=#አዲስ_ዝማሬ ዲ/ን ዘማሪ #ቀዳሜጸጋ_ዮሐንስ #ተወዳጅ_ዝማሬ
New Ethiopian Orthodox Tewahido Church mezmur by Diakon zemari Kedametsega Yohanis "New" mezmur

✟ፊደል ማርያም✟

ትመስሊ ፊደለ ወትወልዲ ወንጌል ወታገምሪ መስቀለ ሀረገ ወይን ሀረገ ወይን አጸደ ወይን አንቲ ማርያም


ፊደል ማርያም
ንባብ አማኑኤል
ትርጓሜውም እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው
ሚስጢሩ ስጋችንን መልበሱ ነው



ፊደል ከሌለ ምንም የለም
ብርቱ ቃላትም አይገኝም
ለመሰባሰብ ለመሆን ቃል
ፍቃደ ፊደል ይፈለጋል
ያቺ ፊደል ድንግል ናት
ከርሷ ቃል የተገኘባት
ይሁን ብላ ስትቀበል
ተዋሃደ በፍጹም ሃይል

አዝ_____________

ከመጀመሪያ ቃል ነበረ
በእግዚአብሄር ዘንድ የነበረ
ቃልም አማኑኤል ነው
ዛሬ ከኛ ጋር የሆነው
እርሱ መልካም ነው ቸር
ከላይ ሳይጎድል የሚኖር
በማርያም እቅፍ ውስጥ ያለው
አማኑዔል እግዚአብሄር ነው

አዝ_____________

አለምን ከፈጠረበት
ተሰቅሎ ያዳነበት
ጥበቡም ረቂቅ ነው
ማያገኙትም ተመራምረው
ከአንዲት ድንግል በቀር
እግዚአብሄር አብን የሚመስል
ብቻ መውለድን የተማረች
ርሱን ስሙት ያለች ማርያም ነች

አዝ______________

ቀድሞ ምሳሌን ያሳየን
አስማምታ ስትፈትል ሀር ወርቅን
ማንም ቢፈትል ሀር ይፈትላል
ከወርቅ ጋራ እንዴት ይስማማል
ምሳሌነቱ ሀር የተባለው
የትስብይቱ በእውነት ትርጏሜው ነው
የተፈተለው የነጠረ ወርቅ
ረቂቅ መለኮት ረቂቅ ነው ጥልቅ

ግጥም እና ዜማ
ዲ/ን ዘማሪ ቀዳሜጸጋ ዮሐንስ